ማሳሰቢያ በሚስጥር የተዘጋጀ ሰርፕራይዝ እባክዎ ፕሮግራሙን በተመለከተ ለክቡር አቶ አባዱላ ገመዳ እና ለቤተሰቦቻቸው ምንም ዓይነት መረጃ ባለመስጠት እንዲተባበሩን በታላቅ አክብሮት እንጠይቃለን ።

VVIP Guest

የመፅሐፍ ምርቃት ጥሪ

የቤተሰባቸውን ታሪክ ፣ የህይወት ውጣውረድ ፣ የጓደኞቻቸው ፣ የስራ ህይወት የቀድሞ ባልደረቦቻቸው ፣ ምስክርነት እና ትውስታ ላይ ተመስርቶ የተጻፈው የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ ምርቃት ሥነ-ሥርዓት ይካሄዳል።
ክቡር አቶ አባዱላ ስለ መፀሀፉ መፃፍ እና የምርቃት ዝግጅቱን የሚያውቁት በዕለቱ አዳራሽ ውስጥ ሲደርሱ ነው። እርስዎም በዚህ ዝግጅት ላይ በጋራ አብረን ሰርፕራይዝ እንድናረጋቸው በክብር ተጋብዘዋል፡፡
ፕሮግራሙ እሮብ ሰኔ 3 ቀን 2018 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል- ላሊበላ አዳራሽ ከቀኑ 9 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት 

ስለመጽሐፉ

በሕይወታችን ውስጥ ትልቁ ደስታ ቤተሰባችንን ማስደሰት ነው። እኔም አባቢን ሁልጊዜ “በምን ትደሰታለህ? ምንስ ይበልጥ ያስደስትሃል? ” እያልኩ ደጋግሜ አጠይቀው ነበር። አሱም በፈገግታ የታጀበ ምላሹን እንዲህ ሲል ይገልጽልኝ ነበር፦
“ልጆቼ አደገው፣ ተምረውና ራሳቸውን ችለው ማየት፤ ከዚያም አልፎ የራሳቸውን ሕይወት መስርተው ለወግ ማዕረግ በቅተው፣ በፈጣሪ ፈቃድ ደግሞ የልጅ ልጅ አሳይተውኝ አያት መሆን ትልቁ ምኞቴና ደስታዬ ነው።” ይለኝ ነበር።
እኔ ግን ከዚህ በዘለለ “አባቢን በምን ላስደስተው እችላለሁ?” የሚለው ጥያቄ ዘወትር በአአምሮዬ ይመላለስ ነበር። በተለያዩ አጋጣሚዎች አባቢን የሚያውቁ ሰዎች ስለ እርሱ መልካምነትና ማንነት ሲያወጉኝ በጥሞና እሰማለሁ። የሚገርመው ነገር፣ ሁሉም የሚመሰክሩት ስለ ስኬታማ የሕይወት ጉዞው ብቻ ሳይሆን፣ ስለ ቅንነቱና ስለ ደግነቱ ጭምር ነበር። በዚህም ምክንያት አባቢን እኔ ከማውቀው በላይ እጅግ የሚወደድና የሚከበር ትልቅ ስብእና እንዳለው ተረዳሁ።
ከዕለታት አንድ ቀን “ለምን ይህንን የአባቴን ተወዳጅ የሕይወት ታሪክ በጽሑፍ አላበረክትለትም?” የሚል ሐሳብ መጣልኝ። እንግዲህ የመጀመሪያው ስጦታዬ ራሴን ችዬ፣ ቤተሰብ መስርቼ አባቴን አያት የማድረጉ ምኞት ተሳክቷል። አሁን ደግሞ ለልደት መታሰቢያ ይሆን ዘንድ፣ የስራ አና የትግል አጋሮቹ፣ ወዳጅ ጓደኞቹ የሰጡትን ምስክርነት ከቤተሰባችን ታሪክ ጋር አዋህጄ ይህንን መጽሐፍ ሳበረክትለት እጅግ የላቀ ደስታ ይሰማኛል።

የመፅሐፍ ምረቃ መርሃ ግብር ጊዜ ሰሌዳ

መድረሻ እና አቀባበል

9:00 – 10:00

የቤተሰብ መድረሻ እና አቀባበል

10:00 – 10:20

የዝግጅቱ መጀመር

10:20 – 10:30

የመክፈቻ ንግግር

10:30 – 10:40

የዶክመንተሪ እይታ

10:40 – 10:55

የአብይ ፍቅረበሉ (ረዳት ደራሲ) ንግግር

10:55 – 11:10

መጽሐፍ ዳሰሳ

11:10 – 11:35

የቤኪ አባዱላ ንግግር

11:35 – 11:50

የክቡር አባዱላ ገመዳ ንግግር

11:50 – 12:15

መጽሐፍ ምረቃ (ማስተዋወቅ)

12:15 – 12:25

መጽሐፍ ሽያጭ

12:25 – 12:55

የምስጋና መርሃ-ግብር

12:55 – 1:05

የልደት በዓል አከባበር እና መዝጊያ

1:05 – 1:15

የፎቶ ፕሮግራም

1:15 – 1:45

እራት ፐሮግራም

1:45

መጽሐፍ ምረቃት ቀን የቀረው
0
ቀናት
0
ሰዓት
0
ደቂቃ
0
ሴኮንድ

አድራሻ

ከእኛ ጋር ተቀላቀሉ

የክብር ስፖንሰሮች

እንገናኝ !!!

በ yeneevent.com የተዘጋጀ